የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዘንድሮው ዓመት በድምቀት ይከበራል።

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው የፊቼ ጫምባላላ በዓል አከባበርን አስመልክቶ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ጃጎ በመግለጫቸው ላለፉት ለሁለት ዓመታት የፊቼ ጫምባላላ በዓል በኮሮና በሽታ ምክንያት በጉዱማሌ እንዳልተከበረና ህዝቡ ግን በየቤቱ እንዳከበረ ገልጾ ዘንድሮ በሲዳማ ብሔር ዘንድ በአደባባይ በጉዱማሌ ለማክበር ከዛም አልፎ በሀገር ደረጃ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቅቋል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም ለፊቼ ጫምባላላ የሚደረግ ክንውኖች ላኦ ወይም ምልከታ፣ ቀኑን ማስታወቅ ወዘተ በአያንቶች የሚደረግና የበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ቅቤ የማጠራቀም፣ የተጣሉትን ማስታረቅ፣ የከብቶች የግጦሽ ሳር ማዘጋጀትና የመሳሰሉ ልዩ ልዩ ክንውኖች በቤተሰብ ደረጃ የሚደረጉ ናቸው ብለዋል።

የፊቼ ጫምባላላ በዓል የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኒስኮ የተመዘገበ የማይዳሰስ ቅርስ ነው ያሉት ኃላፊው በዓሉ ስከበርም እንግዶች በዓሉን ለመታደም ከተለያዩ ሀገራት ይመጣሉ ይህም የቱሪስቶችና ለባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብለው ፊቼ ጫምባላላ በውስጡ የያዛቸው እሴቶች በመኖሩ ይሄንንም የሚገልጽ የፓናል ውይይት በፊቼ ቀን ይካሄዳል ብለዋል።

የፊቼ ጫምባላላ በዓል ብዝሃነትን የሚገልጽ በዓል ነው ይህም የአብሮነት መገለጫ የሆነውን ሻፌታ በአንድነት የሚቆረስ፣ የቄጣላ ክንውን የሚደረገውም በአንድነት ነው ከዚህም ባሻገር ለአካባቢው ጥበቃም ልዩ ትኩረት የሚሰጥበትና አሁን አረንጓዴ አሻራ የሚንለውም ሲዳማ ከጥንት ጀምሮ ይዞ የመጣ እንደሆነና በላላዋ ስርዓት የኮሙኒኬሽን ስርዓትም በጥንትም ያለ ነው በማለት በዓሉን ልዩ ያደርገዋል ብዋል።

የበዓሉን ቀን የሚገልጹት አያንቶች በመሆናቸው ይህም የማክበርያ ቀን ልደርስ ሳምንታት ስቀር ነው ለህዝቡ ይፋ የሚያደርጉት ብለው ይሁን እንጂ በመንግሥት በኩል የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ እንደሆነ በመግለፅ የበዓሉ ባለቤት የህዝብ በመሆኑና የማንንም ጣልቃ ገብነት ስለማያስፈልገው በዓሉን ህዝቡ የሚጠብቅ ብሆንም ያለ አንዳች ችግር በዓሉ እንዲከበር የተለያዩ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሥራውን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ኃላፊው ጨምረው ገልጿል።

በበዓሉ ቀን ከተለያዩ ክልሎች፣ ከፌደራል ሚንስተሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት መሪዎችና የተለያዩ እንግዶች እንዲገኙና ከክልሉ ውጭ ሌሎች ከተማዎች ላይ ጫምባላላን ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።